am_tn/isa/45/13.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ መናገር ቀጥሏል፡፡

ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቻለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ጽድቅ›› የሚያመለክተው ተገቢ የሆነ ሥራ ነው፡፡ ይህም ማለት፣ 1) ተገቢ የሆነውን ነገር እንዲያደርግ ያህዌ ቂሮስን አስነሣው፤ ወይም 2) ቂሮስን በማስነሣቱ ያህዌ ትክክል ነበር ማለት ሊሆን ይችላል፡፡

ቂሮስን አስነሥቻለሁ

ቂሮስን ማስነሣቱ እርሱን ከእንቅልፍ መቀስቀሥ እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡

መንገዱን ሁሉ አስተካክልለታለሁ

ዕንቅፋትን ማስወገዱና ቂሮስ እንዲሳካለት ማድረግ መንገዱን ማስተካከል እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡

ከተማዬን እንደ ገና ይሠራታል

ይህ የሚያመለክተው ኢየሩሳሌምን ነው፡፡

ያለ ክፍያ ወይም ያለ ጉቦ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ክፍያ›› እና፣ ‹‹ጉቦ›› ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ቂሮስ ይህን ሁሉ የሚያደረገው ለገንዘብ አይደለም፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይህንንም የሚያደርገው ለሚያገኘው ገንዘብ ሲል አይደለም››

የሰራዊት ጌታ ያህዌ

ኢሳይያስ 1፥9 ላይ ይህን ሐረግ እንዴት እንደ ተረጐምህ ተመልከት፡፡