am_tn/isa/45/02.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለቂሮስ መናገር ቀጥሏል፡፡

ተራሮችን እደለድላለሁ

የያህዌን ስኬት የሚያሰናክል እንቅፋትን ሁሉ ማስወገዱ በፊቱ ተራሮችን ደልዳላ ማድረግ እንደ ሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡

ተራሮች

በዐውዱ የተጠቀሰው የዕብራይስጥ ቃል ብዙም ጥቅም ላይ የማይውል ሲሆን፣ ትርጒሙም ግልጽ አይደለም፡፡ አንዳንድ ዘመናዊ ትርጒሞች፣ ‹‹አስቸጋሪ ቦታዎች›› ወይም፣ ‹‹ጐርበጥባጣ ስፍራዎች›› ብለዋል፡፡

የብረት መወርወሪያዎች

ይህ የሚያመለክተው የናሱ ደጆች ላይ ያሉትን የብረት ዘንጐች ነው፡፡

በጨለማ ያለውን ንብረት

‹‹በጨለማ›› በምስጢር ቦታ ማለት ነው፡፡ ‹‹ጨለማ ቦታ ያለ ንብረት›› ወይም፣ ‹‹በምስጢር ቦታዎች ያለ ንብረት››