am_tn/isa/44/23.md

714 B

ሰማያት ሆይ ዘምሩ… ክብር በእስራኤል

እዚህ ላይ ኢሳይያስ ያህዌን እንዲያመሰግኑ የሚያዝዛቸው ሰዎች የሆኑ ይመስል ለተለያዩ የፍጥረት ክፍሎች ይናገራል፡፡

የምድር ጥልቆች ሆይ

‹‹ዝቅ ያላችሁ የምድር ክፍሎች›› ይህም ማለት፣ 1) ባለፈው ሐረግ ከተጠቀሱ፣ ‹‹ሰማያት›› ጋር በንጽጽር የሚቀርቡ ዋሻዎችን፣ ወይም ጉድጓዶችን ለመሳሰሉ ዝቅ ያሉ የመሬት ክፍሎችን ያመለክት ይሆናል፡፡ ወይም 2) የሞቱ ሰዎችን የሚያመለክት ሊሆን ይቸላል፡፡