am_tn/isa/44/21.md

1018 B

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ መናገር ቀጥሏል፡፡

ያዕቆብና እስራኤል

ይህ ከያዕቆብና ከእስራኤል የተገኘውን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እናንተ የእስራኤል ዘሮች››

እኔ አልረሳችሁም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ አልረሳችሁም››

ዐመፃህን እንደ ድቅድቅ ደመና፣ ኀጢአትህንም እንደ ጭጋግ አስወግጃለሁ

ሁለቱም ዐረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፡፡ ነፋስ ደመናን በቀላሉና በፍጥነት እንደሚያስወግደው እግዚአብሔር ኀጢአታቸውን ይቀር ብሏል፡፡

ኀጢአትህን እንደ ጭጋግ

ግሡ ባለፈው ሐረግ ተገልጿል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እንደ ጭጋግ ኀጢአትህን አስወግጃለሁ››