am_tn/isa/44/09.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ እየተናገረ ነው፡፡

የሚደሰቱባቸው ነገሮች ከንቱ ናቸው

‹‹ደስ የሚሰኙባቸው ጣዖቶች ከንቱ ናቸው››

ምስክሮቻቸው አያዩም ወይም አያውቁም

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ስለ ጣዖቶቹ ኀይል ምስክር እንደሆኑ የሚናገሩ እነዚህን ጣዖቶች የሚያመልኩ ሰዎችን ነው፡፡ እውነቱን መረዳት አለመቻላቸውን ያህዌ ዕውራን ናቸው ብሏል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ለእነዚህ ጣዖቶች ምስክር በመሆን የሚያገለግሉ ምንም እንደማያውቁ ዕውሮች ናቸው››

ያፍራሉ

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ይዋረዳሉ›› ወይም፣ ‹‹ጣዖቶቻቸው ያሳፍሩዋቸዋል››

አምላክን የሚያበጅ ወይም ጥቅም የሌለውን ጣዖት የሚቀርጽ ማን ነው?

ያህዌ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ጣዖት የሚሠሩትን ለመገሠጽ ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አምላክ የሚሠራ ጥቅም የሌለውን ጣዖት የሚቀርጽ ሞኝ ብቻ ነው››

ጥቅም የሌለውን ጣዖት የሚቀርጽ

‹‹ጥቅም የሌለው›› የሚለው ቃል ጥቅም ካለው ጣዖት ጋር ለማነጻጸር የተነገረ አይደለም፤ ምክንያቱም ጣዖቶች ሁሉ ከንቱ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጥቅም የለሽ ጣዖት የሚቀርጽ››