am_tn/isa/44/08.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡

አትፍራ አትደንግጥ

የእርሱን ማበረታቻ ለማጠናከር ያህዌ በሁለት ተመሳሳይ ገለጻዎች ይጠቀማል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አትፍራ››

አልነገርኃችሁምን፤ ቀድሞንስ አላስታወቅኃችሁምን?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው አሁን የሆነውን አስቀድሞ መናገር የሚችል እርሱ መሆኑን አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ ‹‹ማስታወቅ›› የሚለው ቃል፣ ‹‹መናገር›› ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከረጅም ጊዜ በፊት ነገርኃችሁ››

ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን?

ያህዌ ጥያቄውን ያቀረበው ከእርሱ በቀር አምላክ እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ጥያቄውን በዐረፍተ ነገር መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ከእኔ በቀር አምላክ የለም››

ሌላ ዐለት የለም

ያህዌ እርሱ ሰዎች የሚጠለሉበት ትልቅ ዐለት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህም ማለት ሕዝቡን ለመጠበቅ ኀይል አለው ማለት ነው፡፡