am_tn/isa/44/03.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል

በተጠማ ምድር ላይ ውሃ፣ በደረቅ መሬት ላይ ምንጮች አፈስሳለሁ

ለእስራኤል ሕዝብ መንፈሱን መስጠቱ በተጠማ ምድር ላይ ዝናብ ማዝነብና በደረቅ መሬት ላይ ምንጮች ማፍሰስ እንደ ሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡

የተጠማ ምድር

ደረቅ መሬት የተጠማ ሰው ማለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ደረቅ መሬት››

መንፈሴን በዘርህ ላይ አፈስሳለሁ

መንፈሱን ለሕዝቡ መስጠቱ መንፈሱ እነርሱ ላይ የሚፈስስ ፈሳሽ ነገር መሆኑን ያህዌ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹መንፈሴን ለዘርህ እሰጣለሁ››

በረከቴንም በልጆችህ ላይ

ግሡ ባለፈው ሐረግ ተነግራል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በረከቴን በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ›› ወይም ‹‹በረከቴን ለልጆችህ እሰጣለሁ››

በለመለመ መስክ ላይ እንደ ሣር፣ በምንጭ ዳር እንደ አኻያ ይበቅላሉ

የእስራኤል ሕዝብ መበልጸግና መብዛት ብዙ ውሃ በማግኘቱ እንዳደገ ተክል መሆናቸው ተነግሯል፡፡

አኻያ

አኻያ ቀጫጭን ቅርንጫፎች ያሉት ውሃ አጠገብ የሚያድግ ዛፍ ነው፡፡