am_tn/isa/43/27.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገር ቀጥሏል፡፡ የመጀመሪያው አባትህ ኀጢአት ሠርቷል ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን መሥራች ሲሆን፣ አብርሃምን ወይም ይስሐቅን ነው፡፡

ያዕቆብን ለጥፋት አሳልፌ እሰጣለሁ

እዚህ ላይ፣ ‹‹አሳልፌ›› የሚለው በሌላው ኀይል ሥር ያለ ሰውን ነው፡፡ ‹‹ጥፋት›› የሚለውን በሌላ ቃል መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላት ያዕቆብን ጨርሶ እንዲደመሰስ አደርጋለሁ››

እስራኤልን ለስድብና ለውርደት

ግሡን የዚህ ሐረግ ተጓዳኝ ከሆነው ቀደም ሲል ከነበረ ሐረግ ጋር ማያያዝ ይቻላል፡፡ ‹‹ውርደት›› የሚለውን በሌላ ቃል መተርጐም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ጠላት እስራኤልን እንዲሰድብና እንዲያዋርድ አደርጋለሁ››