am_tn/isa/43/16.md

1.0 KiB

መንገድ የከፈተ… እንደ ጧፍ ኩስታሪ

በእነዚህ ጥቅሶች ኢሳይያስ እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ፣ ግብፃውያን ግን እንዲሰጥሙ ያህዌ ባሕሩን የከፈተበትን ከግብፅ መውጣት በኃላ የነበረውን ሁኔታ እያመለከተ ነው፡፡ የዐረፍተ ነገሩን ትርጒም የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡

በአንድነት ወደቁ፤ ከእንግዲህ አይነሡም

መሞት መሬት ከመውደቅ ጋር ተመሳስሎአል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሁሉም በአንድነት ሞቱ፤ ከእንግዲህ በሕይወት አይኖሩም››

ጠፉ፤ እንደ ጧፍ ኩስታሪ ረገፉ

የሕዝቡ መሞት ከሚጠፋ ጧፍ ጋር ተመሳስሎአል፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ሰው የሚነድደውን ሻማ እንደሚያጠፋ ሕይወታቸው አብቅቷል››