am_tn/isa/43/10.md

1.7 KiB

እናንተ… የእኔ አገልጋይ

‹‹እናንተ›› ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው የእስራኤልን ሕዝብ ነው፡፡ ‹‹የእኔ አገልጋይ›› ጠቅላላ መንግሥቱን ያመለክታል፡፡

ከእኔ በፊት… ከእኔ በኃላ

በዚህ መልኩ መናገሩ ከእርሱ በፊት የነበረና ከእርሱ በኃላም እንደሚኖር ያህዌ እየተናገረ አይደለም፡፡ እርሱ ዘላለማዊ ሲሆን፣ ሕዝቡ የሚያመልኳቸው አማልክት ግን አለመሆናቸውን እያረጋገጠ ነው፡፡

ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም

እዚህ ላይ፣ ‹‹አልተሠራም›› ሲል ያህዌ ሕዝቡ ስለሠሩዋቸው ጣዖቶች እየተናገረ ነው፡፡ ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አሕዛብ ካሠሩዋቸው ጣዖቶች አንዱ እንኳ ከእኔ በፊት አልተሠሩም››

ከእኔም በኃላ አይኖርም

‹‹ከእነዚህ አማልክት አንዱም ከእኔ በኃላ አይኖርም››

እኔ፣ እኔ ያህዌ ነኝ

‹‹እኔ›› የሚለው ቃል የተደገመው አጽንዖቱ ያህዌ ላይ እንዲያተኩር ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹እኔ ብቻ ያህዌ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እኔ ራሴ ያህዌ ነኝ››

ከእኔ ሌላ አዳኝ የለም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አዳኝ እኔ ብቻ ነኝ›› ወይም፣ ‹‹እናንተን ማዳን የምችል እኔ ብቻ ነኝ››