am_tn/isa/43/04.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በዐይኔ ፊት ብርቅና ክቡር ስለሆንህ

‹‹ብርቅ›› እና፣ ‹‹ክቡር›› የተሰኙት ቃሎች በመሠረቱ ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ያህዌ ሕዝቡን ምን ያህል እንደሚወድ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በእኔ ዘንድ በጣም የተወደድህ ስለሆነ››

ስለዚህ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ

ሁለቱም ሐረጐች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ስለዚህ በአንተ ፈንታ ጠላት ሌሎች መንግሥታትን ድል እንዲያደርግ አደርጋለሁ››

ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ አንተንም ከምዕራብ እሰበስባለሁ

‹‹ምሥራቅ›› እና ‹‹ምዕራብ›› የተሰኙት አቅጣጫዎች ከሁሉም ቦታ ማለት ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አንተንና ልጆችህን ከሁሉም ቦታ አመጣለሁ››