am_tn/isa/43/02.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ያህዌ ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በውሃ ውስጥ ስታልፍ አያሰጥምህም… በእሳት ውስጥ ስትሄድ አያቃጥልህም፡፡

ሰዎች ላይ የሚደርስ መከራና ችግር የሚያልፉበት ጥልቅ ውሃና እሳት እንደሆነ ያህዌ ይናገራል፡፡ ‹‹ውሃ›› እና፣ ‹‹እሳት›› ምሳሌያዊ ሲሆኑ ማንኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ ያመለክታሉ፡፡

በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው አያሰጥምህም፡፡

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች በመሠረቱ ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፤ ያህዌ ከእነርሱ ጋር ከሆነ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡

አያቃጥልህም

ይህን በሌላ መልኩ መግለጽ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በፍጹም አይፈጅህም››

ግብፅ ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኩሽና ሳባንም በአንተ ፈንታ ሰጥቻለሁ፡፡

እነዚህ ሁለት ሐረጐች ተመሳሳይ ትርጒም አላቸው፤ እስራኤልን ሳይሆን የእስራኤል ጠላቶች እነዚህን መንግሥታት ድል እንዲያደርጉ ያህዌ እንደ ፈቀደ አጽንዖት ይሰጣል፡፡

ሳባ

ይህ የአገር ስም ነው፡፡