am_tn/isa/42/14.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ከድሮ ዘመን ጀምሮ ጸጥ ብያለሁ፣ ዝም ብያለሁ ራሴንም ገድቤአለሁ

እነዚህ ሁለት መሥመርች አንድ ዓይነት ትርጉም አላቸው፡፡ የእግዚአብሔር አለመንቀሳቀስ እንደ ጸጥታና ዝምታ ተገልጾአል፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)

ዝም ብያለሁ ራሴንም ገድቤአለሁ

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ትርጉማቸው አንድ ሲሆን እግዚአብሔር ራሱን ከእንቅስቃሴ እንደ ገታ ያመለክታሉ፡፡ አት፡- "ምንም ከማድረግ ራሴን ገትቼአለሁ' (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)

ምጥ እንደያዛት ሴት እጮኻለሁ … አቃስታለሁ ትንፋሼም ቁርጥ ቁርጥ ይላል

እንደሚጮህ ተዋጊ የእግዚአብሔር እንቅስቃሴ ከምጥ ህመም የተነሣ ከምትጮህ እርጉዝ ሴት ጋር ተነጻጽሮአል፡፡ ከተወሰነ የዝምታ ጊዜ በኋላ በድነገት የሚሆንን አይቀሬ እንቅስቃሴ ያጎላል፡፡ (ዘይአዊ ንግግር ተመልከት)

ተራሮችን አፈርሳለሁ … ረግረጉን አደርቃለሁ

ጠላቶቹን ለማጥፋት ያለውን ታላቅ ኃይል ለመግለጽ እግዚአብሔር ይህን ስዕላዊ ቋንቋ ይጠቀማል። (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ረግረግ

ረግረግ ለስላሳ መሬት፣ ውኃ ያቆረበት እርጥብ መሬት ነው፡፡