am_tn/isa/42/05.md

1.7 KiB

ሰማያትን የፈጠረ፣ የዘረጋቸውም፣ ምድርን የፈጠረ

ሰማያትና ምድር እንደ ጨረቅ የዘረጋቸው እንደሆነ አድርጎ ነቢዩ ስለ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን መፍጠር ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በእርስዋ ላይ ላሉ ሰዎች እስትንፋስን፣ በእርስዋም ለሚኖሩ ሕይወትን የሚሰጥ

በመሠረቱ እነዚህ ሐረጎች የሚናገሩት አንድ ነገር ሲሆን እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ሕይወት እንደሚሰጥ አጉልተው ይናገራሉ፡፡ እስትንፋስ የሚለው ቃል ለሕይወት ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "በምድር ለሚኖሩ ሰዎች ሕይወትን ይሰጣል' (አጓዳኝነትና ምትክ ስም ተመልከት)

ጠርቼሃለሁ

በዚህ ውስጥ "አንተ' የሚለው የእግዚአብሔርን ባሪያ ያመልክታል፡፡ (የ"አንተ' ልዩ ልዩ አጠቃቀሞ ተመልከት)

ለሕዝብ ኪዳን አድርጌህ …

በዚህ ስፍራ "ኪዳን' የሚለው ቃል ኪዳኑን ለመሠረተው ወይም ተፈጻሚ ላደረገው ምትክ ስም ነው፡፡ አት፡- በሕዝቡ ዘንድ የኪዳኑን አስፈጻሚ አደርግሃለሁ … (ምትክ ስም ተመልከት)

ለአሕዛብ ብርሃን

ለአሕዛብ በጨላማ ስፍራ የሚያበራ ብርሃን እንደሚያደርገው በሚመስል መልኩ እግዚአብሔር ባሪያውን ሕዝቦችን ከእስራት የሚፈታ እንደሚያደርገው ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)