am_tn/isa/41/25.md

2.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል

አንዱን አነሣሁ

እግዚአብሔር አንድን ሰው መሾሙን ያንን ሰው ወደ ላይ እንዳነሣ አድርጎ ይናገራል፡፡ አት፡- "አንዱን ሾምሁ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ከፀሐይ መውጫ

ይህ ፀሐይ ወደ ምትወጣበት አቅጣጫ ወደ ምሥራቅ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ከምሥራቅ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ስሜን የሚጠራ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እንዲሳካለት እግዚአብሔርን የሚለምን ሰው 2) እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሰው

ገዢዎችን ይረጋግጣል

የሌሎች ሕዝቦች ገዢዎችን ማሸነፍ ከእግር በታች እነርሱን መርገጥ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ገዢዎችን ድል ያደርጋል' (ሰስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ጭቃ እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪ

እግዚአብሔር ይኼ ሰው ሌሎች ገዢዎችን የሚረግጥበትን መንገድ ከውኃ ጋር ለማደባለቅ ሸክላ ሠሪ ጭቃን ከሚረግጥበት መንግድ ጋር ያስተያያል፡፡ (ዘይቤአዊ አነጋገር ተመልከት)

እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው ማን ነው? "እውነት ነው' እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው?

እግዚአብሔር ሕዝቡ በሚያመልካቸው ጠዖታት ላይ ለመሳለቅ እነዚህን አሳብ ገላጭ ጥያቄዎች ይጠቀማል፡፡ የተጠቆሙ መልሶች 1) ጣዖታት እነዚህን ነገሮች አላደረጉም 2) እነዚህን ያደረገ እግዚአብሔር ብቻ ነው። አት፡- "እናውቅ ዘንድ ከጣዖታት መካከል ማንም ይህንን ከጥንት አላስታወቀም። ‘እውነት ነው’ እንል ዘንድ ከመካከላቸው ማንም አስቀድሞ አልተናገረም።' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ ተመልከት)

በእውነቱ ከመካከላቸው ማንም አልተናገረም፣ አዎ፣ ምንም ስትሉ የሰማ የለም

"በእውነቱ ከጣዖታት መካከል ማንም አልተናገረም፡፡ በእውነቱ ጣዖታት ምንም ስትሉ የሰማ የለም'