am_tn/isa/41/14.md

3.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አንተ ትል ያዕቆብ፣ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ

በዚህ ስፍራ ያዕቆብ እና የእስራኤል ሰዎች ማለት ተመሣሣይ ነገር ነው፡፡ አት፡- "ትል የምትመስሉ የእስራኤል ሰዎች ሆይ' (የሁለት ነገሮች ተመሣሣይነት ተመልከት)

አንተ ትል ያዕቆብ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ሌሎች ሕዝቦች የእስራኤልን ሕዝብ በሚመለከት ያላቸውን አስተያየት ያመለክታል ወይም 2) ይህ ራሳቸው እስራኤላውያን ስለ ራሳቸው ያላቸውን አስተያየት ያመለክታል፡፡ ትል እንደሆኑ አድርጎ እግዚአብሔር ስለ ትንሽነታቸው ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እያወጀ ያለውን ነገር እርግጠኝነት ለመግለጽ እግዚአብሔር በራሱ ስም ይናገራል፡፡ በኢሳይያስ 30፡1 እንዳለው ተርጉም፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው' ወይም "እኔ፣ እግዚአብሔር ያወጅኩት ይህ ነው' (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

የእስራኤል ቅዱስ

ይህንን ሐረግ በኢሳይያስ 1፡4 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

እኔ እንደተሳለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ … ኮረብቶችን እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ

ሕዝቡን ተራራሮችን ደልዳላ የሚያደርግ ስለታም ማሄጃ እንደሚያደርግ ዓይነት እስራኤል ጠላቶቹን እንዲያሸነፍ እንደሚያስችለው እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የተሳለ ስለታም ማሄጃ

ፍሬውን ከገለባው ለመለየት እንድ ሰው ስንዴ ላይ የሚጎትተው የሾሉ ብረቶች ያሉት ነገር ነው፡፡

በሁለት ወገን የተሳለ

ይህ ከስለታም ማሄጃ ጋር የሚያያዙትን የሾሉ ብረቶች ጠርዝ ያመለክታል፡፡ በሁለት ወገን የተሳሉ ናቸው ማለት በጣም ስለታም ናቸው ማለት ነው፡፡

ተራሮችን ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ

ይህ ድርብ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ ተራራሮች እህልን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ስዕላዊ ንግግር ነው፤ እህልን ማሄድ ደግሞ በአቅራቢያዋ የሚገኙ ኃያላን የሆኑ ጠላት ሕዝቦችን እስራኤል እንደምታሸነፍ ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ አት፡- "እንደ ተራሮች ጠንካሮች መስለው ቢታዩም ጠላቶቻችሁን እንደ እህል ታሄዷቸዋለችሁ፣ ታደቅቋቸውማላችሁ፡፡' (ስዕላዊ ንግግር እና ገነትና ማጠቃለይ ተመልከት፡፡)

ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸውማለህ

ኮረብቶች በእስራኤል አቅራቢያ የሚገኙ ኃያላን የሆኑ ጠላት ሕዝቦችን የሚያመልከት ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ ሕዝቡ እህሉን ካሄዱት በኋላ ነፋሱ ገላባውን ጠርጎ እንዲወስደው ማድረግ የሚገባቸው መሆኑ እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን እንዲያጠፋ ሊፈቅዱለት የሚገባ ለመሆኑ ስዕላዊ ንግግር ነው፡፡ (ስዕላዊ ንግግርና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)