am_tn/isa/41/05.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ደሴቶች … የምድር ዳርቾች

እነዚህ ሐረጎች በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላሉ፡፡ አት፡- "በደሴቶች የሚኖሩ ሰዎች … በምድር ዳርቾች የሚኖሩ ሰዎች' (ምትክ ስም ተመልከት)

ደሴቶች

በኢሳይያስ 41፡1 በተረጎምኸው መሠረት መተርጎም ትችላለህ፡፡

የምድር ዳርቾች

በምድር በጣም ሩቅ የሆኑ ቦታዎች ምድር የምታበቃባቸው ቦታዎች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "የምድር በጣም ሩቅ ቦታዎች' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ቀረቡ መጡም

እነዚህ ሁለቱ ተመሣሣዮች ሕዝቡ በአንድነት ተሰበሰቡ የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ አት፡- "በአንድነት መጡ' (የሁለት ነገሮች ተመሣሣይነት ተመልከት)

የብረት ቅርጽ ማውጫ

ሰው በመዶሻ ብረትን ቅርጽ የሚያስዝበት የብረት ማስቀመጫ

አንጥረኛውን … አለ

በዚህ ስፍራ ማንጠር የሚለው ቃል ሠራተኞቹ ጣዖቱን መሥራት እንደጨረሱ ወርቁን ከእንጨቱ ጋር የማጠበቅን ሂደት ያመለክታል፡፡

እንዳይንቀሳቀስም በምስማር ቸነከሩት

በዚህ ውስጥ እርሱ የሚለው የሠሩትን ጣዖት ያመለክታል፡፡