am_tn/isa/41/01.md

2.2 KiB

በፊቴ በጸጥታ አድምጡ

በዚህ ወስጥ "እኔ' የሚለው እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡

እናንተ ደሴቶች

ይህ በደሴቶችና አዋሳኝ መሬቶች ወይም ከሜዲትራኒያን ባሕር ማዶ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ (ምትክ ስምና በስፍራው ለሌለ ወይም እንደ ሰው ለተወሰደ ግዑዝ ነገር መናገር ተመልከት)

ኃይላቸውን ያድሱ

ይህንን ሐረግ በኢሳይያስ 40፡31 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ይቅረቡ በዚያን ጊዜም ይናገሩ፣ ለክርክርም በአንድነት እንቅረብ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለተኛው ለመጀመሪያው ምክንያትን ያቀርባል፡፡ አት፡- "ይናገሩና ከእኔ ጋር ይከራከሩ ዘንድ ይቅረቡ' (አጓዳኝነት ተመልከት)

አንዱን ከምሥራቅ ያስነሳው በጽድቅም ለአገልገሎቱ የጠራው ማን ነው?

ይህንን ገዢ ከምሥራቅ ድል አድራጊ አድርጎ ያስነሣው እርሱ እንደሆነ ለማጉላት እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "ይህን ኃያል ገዢ ከምሥራቅ የጠራሁት በመልካሙ አገልግሎቴም ላይ የሾምኩት እኔ ነኝ' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

አሕዛብንም አሳልፎ ሰጠው

"አሕዛብን አሳልፌ ሰጠሁት' ወይም "እነዚህን ነገሮች ያደረገ እርሱ አሕዛብን አሳልፎ ሰጠው'

ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አደረጋቸው

እነርሱን ትቢያና የተጠረገ እብቅ እንዳደረገ መነገሩ የእነዚህ ሕዝቦች ሰዎች የሠሩትን ሁሉ ፈጽሞ ለማጥፋቱ ስዕላዊ ንግግርና ግነት ነው፡፡ ከምሥራቅ የሆነው የእርሱ ሠራዊት አሕዛብን ድል ይነሣሉ በቀለሉም ይበትኑአቸዋል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር፣ ዘይቤአዊ ንግግርና ግነትና ማጠቃለያ ተመልከት)