am_tn/isa/40/29.md

1.1 KiB

ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፣ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው እግዚአብሔርም ብርታት የሌላቸውን እንደሚያበረታ ያጎላሉ፡፡ (አጓዳኝነት ተመልከት)

ኃይልን ይሰጣል

"እግዚአብሔር ኃይል ይሰጣል'

እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ

የሕዝቡ ከእግዚአብሔር ኃይል መቀበል ሕዝቡ ንስር እንደሚበርር መብረር እንደቻለ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ንስር ብዙ ጊዜ ለብርታትና ለኃይል ምልክት ሆኖ ጥቅም ላይ የሚውል ወፍ ነው፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ይሮጣሉ አይታክቱም፣ ይሄዳሉ አይደክሙም

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው፡፡ ከእግዚአብሔር ኃይል የተቀበሉ ሰዎች ሳይደክማቸው መሮጥና መሄድ እንደቻሉ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (አጓዳኝነትና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)