am_tn/isa/40/27.md

2.2 KiB

ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ … ፍርዴ … ለምን ትላለህ? … ትናገራለህ'?

ጥያቄው እየተናገሩ ያሉትን መናገር እንደሌለባቸው ያጎላል፡፡ አት፡- "የእስራኤል ሕዝብ ሆይ … ፍርዴ … አትበል' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ … ለምን ትላለህ? ትናገራለህ?

እነዚህ ሁለቱም ሐረጎች የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡ አት፡- "የእስራኤል ሕዝብ ሆይ ለምን ትላለህ' (የሁለት ነገሮች ተመሣሣይነት ተመልከት)

መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች

የእግዚአብሔር የሚሆንባቸውን አለማወቅ እግዚአብሔር የሚጓዙበትን መንገድ እንደማያይ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "የሚሆንብንን እግዚአብሔር አያውቅም' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

አምላኬ ስለ ፍርዴ ግድ የለውም

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ሌሎች በእኔ ላይ ስለሚያደርጉት ኢፍትሐዊ ነገር አምላኬ ግድ የለውም' ወይም 2) "አምላኬ ለእኔ ፍትሕን ለማድረግ ግድ የለውም'

አላወቅህምን? አልሰማህምን?

ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ማወቅ እንዳለበት ለማጉላት ኢሳይያስ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማል፡፡ እነዚህን በኢሳይያስ 40፡21 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡ አት፡- "በእርግጥ ታውቃላችሁ ሰምታችኋልም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

የምድር ዳርቻ

በምድር በጣም ሩቅ የሆኑ ቦታዎች ምድር የምታልቀበት ቦታዎች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ እነዚህ ሐረጎች ስዕላዊ ንግግር ይፈጥራሉ በዳርቻዎችም መካከል ያሉትን ቦታዎች ሁሉ ያመለክታል፡፡ አት፡- "በጣም ሩቅ የሆኑ የምድር ቦታዎች' ወይም "መላው ምድር' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)