am_tn/isa/40/25.md

1.7 KiB

እመሳሰለው ዘንድ ከማን ጋር አስተያያችሁኝ?

የሚመስለው ማንም እንደሌለ ለማጉላት እግዚአብሔር ሁለት ተመሣሣይ አሳብ ገላጭ ጥያቄዎችን ይጠቀማል፡፡ አት፡- "እኔን ልታስተያዩ የምትችሉበት ማንም የለም፡፡ የምመስለው ማንም የለም፡፡' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና አጓዳኝነት ተመልከት)

እነዚህን ከዋክብት ሁሉ የፈጠረ ማን ነው?

ይህ እግዚአብሔር ነው የሚል ምላሽ የሚጠብቅ መሪ ጥያቄ ነው፡፡ አት፡- "እነዚህን ሁሉ ከዋክበት እግዚአብሔር ፈጠራቸው!' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ሰልፋቸውን ይመራል

በዚህ ስፍራ "ሰልፍ' የሚለው ቃል ወታደራዊ ሰልፍን ያመለክታል፡፡ ከዋክበቱ እግዚአብሔር እንዲገለጡ የሚያዝዛቸው ወታደሮች እንደሆኑ አድርጎ ነቢዩ ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በኃይሉ ታላቅነትና በኃይሉ ብርታት

"የኃይሉ ታላቅነት' እና "የኃይሉ ብርታት' የሚሉት ሐረጎች የእግዘአብሔርን ኃይል የሚያጎሉ ሁለት ተመሣሣይ ነገሮችን ይመሠርታሉ፡፡ አት፡- "በታላቅ ኃይሉና በብርቱ ኃይሉ' (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)

አንዱም አይጠፋም

አሉታዊው አሳብ አዎንታዊዉን ያጎላል፡፡ አት፡- "እያንዳንዱ ይኖራል' (ሁኔታን በማንበብ ላይ የተመሠረተ ትንቢት ተመልከት)