am_tn/isa/40/23.md

1.5 KiB

ዝቅ ያደርጋል

"እግዚብሔር ዝቅ ያደርጋል'

ገና እንደ ተተከሉ … እነርሱም ደረቁ

አዳዲስ ተክሎች ሞቃታማ ነፋስ ሲነፍስባቸው እንደሚደርቁ አለቆች በእግዚአብሔር ፊት ተስፋ የሌላቸው እንደሆኑ ነቢዩ ይናገራል ፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

እነርሱ ገና እንደተተከሉ፣ ገና እንደተዘሩ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ የሚናገሩት አንድ ነገር ሲሆን ተክሉ ወይም ዘሩ መሬት ውስጥ የተተከለበትን ነጥብ ያመለክታሉ፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "አንድ ሰው ወዲያው እንደተከላቸው … አንድ ሰው ወዲያው እንደዘራቸው' (አጓዳኝነትና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ነፋስ እንደ እብቅ ጠርጎ ወሰዳቸው

አለቆችን እንደ ተክል እግዚአብሔርን ደግሞ እንዲጠወልጉ በሚያደርግ ነፋስ የገለጻቸው ስዕላዊ ንግግር በዚህ ዘይቤአዊ ንግግር ቀጥሏል፡፡ ነፋስ እብቅን ጠርጎ እንደሚወስድ የእግዚአብሔር የፍርድ ነፋስ የደረቁትን ተክሎች በቀላሉ ያስወግዳቸዋል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)