am_tn/isa/40/21.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለእግዚአብሔር ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አላወቃችሁምን? አልሰማችሁምን? ከመጀመሪያው አንስቶ አልተወራላችሁምን? ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?

እንደ ፈጣሪነቱ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ሕዝቡ ማወቅ እንደሚገባቸው አጽንዖት ለመስጠት ኢሳይያስ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማል፡፡ አት፡- "እናንተ በእርግጥ አውቃችኋል ሰምታችኋልም! ከመጀመሪያው አንስቶ ተነግሮአችኋል፤ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አስተውላችኋል!' (አሳብ ገላጭ ጥያቄና አጓዳኝነት ተመልከት)

ከመጀመሪያ አንስቶ አልተወራላችሁምን?

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ከመጀመሪያው አንስቶ ሰዎች አላወሩላችሁምን?' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ

ምድር እግዚአብሔር መሠረት የጣለላት ሕንፃ እንደሆነች አድርጎ እግዚአብሔር ምድርን እንደፈጠራት ነቢዩ ይናገራል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ አንስቶ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በምድር ክበብ ላይ የሚቀመጠው

እግዚአብሔር ምድርን መግዛቱን፣ እግዚአብሔር ከምድር ከፍ ብሎ ዙፋን ላይ እንደተቀመጠ አድርጎ ነቢዩ ይናገራል፡፡

በእርስዋም የሚኖሩት በፊቱ እንደ አንበጣ ናቸው

ነቢዩ እግዘኢብሔር ሰዎችን የሚያይበትን መንገድ ሰዎች አንብጣን ከሚያዩበት መንገድ ጋር ያስተያያል፡፡ አንበጦች ለሰዎች ትንሽ እንደሆኑ እንዲሁ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ትንሽና ደካማ ናቸው፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖሪያ የሚዘረጋቸው

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሣሣይ ትርጉም አላቸው፡፡ እግዚአብሔር ሰማያትን የፈጠረው በውሰጡ ለመኖር ድንኳን እንደሚተክል እንደሆነ አድርጎ ነቢዩ ይናገራል፡፡ አት፡- "ሰው በቀላሉ መጋረጃ እንደሚዘረጋ ወይም በውስጡ ለመኖር ድንኳን እንደሚተክል ሰማያትን ዘረጋ' (አጓዳኝነትና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)