am_tn/isa/40/15.md

1.3 KiB

ተመልከት … እይ

እነዚህ ቃላት በሚከተለው ላይ አጽንዖት ይጨምራሉ፡፡

አሕዛን በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም ላይ እንዳለ ትቢያ ተቆጥረዋል

ነቢዩ፣ አሕዛብ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ትንሽና እዚህ ግቡ የማይባሉ መሆናቸውን ለማጉላት ከውኃ ጠብታና ከትቢያ ጋር ያስተያያቸዋል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

በገንቦ እንዳለች ጠብታ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ገንቦ ውስጥ ጠብ ያለ የውኃ ጠብታ ወይም 2) ከገንቦው ወደ ወጪ ጠብ ያለ የውኃ ጠብታ

በሚዛን ላይ እንዳለ ትቢያ ተቆጥረዋል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር በሚዛን ላይ እንዳለ ትቢያ ይቆጥራቸዋል፡፡' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

በእርሱ ዘንድ እንደሌለ ነገር ተቆጥረዋል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እርሱ እንደሌለ ነገር ይቆጥራቸዋል' (አድጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)