am_tn/isa/40/09.md

1.6 KiB

የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ

ከተራራ ጫፍ የምሥራች የምታወጅ መልእክተኛ እንደሆነች አድርጎ ጸሐፊው ስለ ጽዮን ይናገራል፡፡ (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)

ከፍ ወደ አለ ተራራ ውጪ

የሚያውጁትን ብዙ ሰዎች መስማት እንዲችሉ መልእክተኞች እንደ ተራራ ባለ ከፍ ባለ መሬት ላይ ብዙ ጊዜ ይቆማሉ፡፡ (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ጽዮን

ይህ በጽዮን የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አት፡- "እናንተ የጽዮን ሰዎች' (ምትክ ስም ተመልከት)

የምስራች የምታመጪ ኢየሩሳሌም ሆይ

ጸሐፊው ኢየሩሳሌም የምስራች የምታውጅ መልእክተኛ እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ (ግዑዝ ነገር እንደ ሰው ማየትን ተመልከት)

ክንዱ ስለ እርሱ ይገዛል

በዚህ ስፍራ ክንድ የእግዚአብሔርን ኃይል ይወክላል፡፡ አት፡- "በታላቅ ኃይል ይገዛል' (ምትክ ስም ተመልከት)

ዋጋው ከእርሱ ጋር ነው … ያዳናቸው በፊቱ ይሄዳሉ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ ተመሣሣይ ነገር ይናገራሉ፡፡ ያዳናቸው እነርሱ ዋጋው ናቸው፡፡ አት፡- "ያዳናቸውን እንደ ዋጋው ከራሱ ጋር ያመጣቸዋል' (አጓዳኝነት ተመልከት)