am_tn/isa/40/06.md

1.8 KiB

ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው

"ሣር' የሚለው ቃል ሕዝቡን ያመለክታል፡፡ ሁለቱም ፈጥነው ስለሚሞቱ ተናጋሪው ሰዎች እንደ ሣር እንደሆኑ ይናገራል፡፡ አት፡- "ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የኪዳናቸው ታማኝነት እንደ ሜዳ አበባ ነው

ተናጋሪው ሕዝቡ ለኪዳናቸው ያላቸውን ታማኝነት ከአበቦች ማበብና ፈጥኖ መሞት ጋር ያስተያያል፡፡ "ታማኝነት' የሚለው የነገር ስም "ታማኝ' በሚል ሊገልጽ ይችላል፡፡ "የኪዳን ታማኝነት' የሚለውን በኢሳይያስ 16፡5 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "የሜዳ አበባ ፈጥኖ እንደሚሞት ለኪዳን ታማኝ መሆንን ፈጥነው ያቆማሉ' (ዘይቤአዊ ንግግርና የነገር ስም ተመልከት)

የኪዳን ታማኝነት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) የኪዳን ታማኝነት ወይም 2) ውበት

የእግዚአብሔር እስትንፋስ ሲነፍስበት

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) "እግዚአብሔር እስትንፋሱን ሲያነፍስበት' ወይም 2) "እንዲነፍስበት እግዚአብሔር ነፋስ ሲልክ፡፡'

ሰው ሣር ነው

ሁለቱም ፈጥነው ስለሚሞቱ ተናጋሪው ሰዎች ሣር እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል

ቃሉ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖር አድርጎ እግዚአብሔር የተናገረው ለዘላለም እንደሚኖር ተናጋሪው ይናገራል፡፡ (ሰስዕላዊ ንግግር ተመልከት)