am_tn/isa/40/03.md

2.7 KiB

የሚጮኽ ድምጽ

ድምጽ የሚለው "ቃል' የሚጮኸውን ሰው ይወክላል፡፡ አት፡- "የሚጮኽ ሰው' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፣ለአምላካችንም ጎዳና በበረሃ አስተካክሉ

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተጓዳኝ ሲሆኑ በመሠረቱ የሚናገሩትም አንድ ዓይነት ነገር ነው፡፡ ለአግዚአብሔር እርዳታ የሕዝቡ ራሱን ማዘጋጀት እንዲሄድበት ለእግዚአብሔር መንገድ ማዘጋጀት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (አጓዳኝነትና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በረሃ

ይህንን ቃል በኢሳይያስ 35፡1 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፣ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል

እነዚህ ሐረጎች ሕዝቡ እንዴት ለእግዚአብሔር ጎዳና ማዘጋጀት እንዳለባቸው ያብራራሉ፡፡ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጹ ይችላል፡፡ አት፡- "ሸለቆውን ሁሉ ከፍ አድርጉ፣ ተራራውንና ኮረብታውን ሁሉ ዝቅ አድርጉ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል

ሸለቆውን ከተቀረው መሬት ጋር የተስተካከለ ማድረግ ሸለቆውን ከፍ ማድረግ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ሸለቆው ሁሉ ይሞላል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ጠማማውም መሬት ይቃናል፣ ስርጓጉጡም ቦታ ሜዳ ይሆናል

እነዚህ ሐረጎች ሕዝቡ እንዴት ለእግዚአብሔር ጎዳና ማዘጋጀት እንዳለባቸው ያብራራሉ፡፡ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አት፡- "ጠማማውን መሬት አቃኑ፣ ስርጓጉጡንም ቦታ ሜዳ አድርጉ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ እና መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ ተመልከት)

የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ክብሩን ይገልጻል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና

"አፍ' የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ራሱን ይወክላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ተናግሮአልና' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)