am_tn/isa/40/01.md

2.0 KiB

አጽናኑ፣ አጽናኑ

አጽናኑ የሚለው ቃል አጽንዖት ለመስጠት ተደግሞአል፡፡

ይላል አምላካችሁ

በዚህ ውስጥ "አናንተ' የሚለው የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንዲያጽናኑ ነቢዩ የሚነግራቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ (የ "አንተ' ልዩ ልዩ አጠቃቀሞች ተመልከት)

ለኢየሩሳሌም በፍቅር ልብ ተናገሩ

ነቢዩ ስለ ኢየሩሳሌም እግዚአብሔር ይቅር እንዳላት ሴት አድርጎ ይናገራል፡፡ ኢየሩሳሌምም በከተማይቱ ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ትወክላለች፡፡ አት፡- "ለኢየሩሳሌም ሕዝብ በፍቅር ልብ ተናገሩ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየትና ምትክ ስም ተመልከት)

አውጁላት … ጦርነትዋ … ኃጢአትዋ … ተቀብላለች … ኃጢአትዋ

በዚህ ውስጥ የሚገኘው ተውላጠ ስም ኢየሩሳሌምን ያመልከታል፣ ነገር ግን "የኢየሩሳሌም ሕዝብ' እንደ አማራጭ ትርጉም ከተወሰደ ሊቀየር ይችላል፡፡ አት፡- "አውጁላቸው … ጦርነታቸው … ኃጢአታቸው … ተቀብለዋል … ኃጢአታቸው' (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሦሥተኛ መደብ ተመልከት)

ጦርነትዋ

"ጦርነት' የሚለው ቃል ሊያመለክታቸው የሚችሉ ትርጉሞች 1) ወታደራዊ ውጊያ ወይም 2) የግዳጅ የጉልበት ሥራ፡፡

ኃጢአትዋ ተሰረየ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ኃጢአትዋን ይቅር አላት' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ከእግዚአብሔር እጅ

በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው እግዚአብሔርን ራሱን ይወክላል፡፡ አት፡- "ከእግዚአብሔር' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)