am_tn/isa/38/16.md

1.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሕዝቅያስ የተጻፈ ጸሎቱን ይቀጥላል፡፡

ሕይወቴ ተመልሶ ይሰጠኝ እንደሆነ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕይወቴን መልስህ ትሰጠኝ እንደሆነ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ከጥፋት ጉድጓድ

ሕዝቅያስ አልሞተም ነገር ግን እያጣጣረ ነበር፡፡ ይህ እግዚአብሔር ከጣር እንዳዳነው ያመልክታል፡፡ የዚህ አሳብ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መሆን ይችላል፡፡ አት፡- "ከጣርና ወደ ጥፋት ጉድጓድ ከመውረድ' ወይም "ስለዚህ አልሞትኩም' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልሆነ መረጃ)

ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጥለሃልና

ሕዝቅያስ፣ እግዚአብሔር ኃጢአቱን ይቅር ማለቱን እግዚአብሔር ወደ ኋላው እንደወረወረውና እንደረሳው ቁስ ነገር አድርጎ ይናገራል፡፡ አት፡- "ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ብለሃልና ከእንግዲህም ወዲያ አታስበውምና' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)