am_tn/isa/38/14.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሕዝቅያስ የተጻፈ ጸሎቱን ይቀጥላል፡፡

እንደ ጨረባ ተንጨጫሁ፣ እንደ ርግብም አጉተመተምኩ

ሁለቱም ሐረጎች ተመሣሣይ ነገር ይናገራሉ፣ የሕዝቅያስ ጩኸቶች ምን ያህል አሳዛኝ አንደሆነም ያጎላሉ፡፡ ጨረባና ርግብ የወፍ ዓይነት ናቸው፡፡ አት፡- "ጩኸቶቼ አሳዛኝ ናቸው–የጨረባ ጫጫታና የርግብ ማጉተምተም ዓይነት ድምጽ ያሰማሉ' (አጓዳኝነትና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ዓይኖቼ

በዚህ ስፍራ ወደ አንድ ነገር መመልከቱን ለማጉላት "ዓይኖቼ' በማለት ወደ ራሱ ያመለክታል፡፡ አት፡- "እኔ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

ወደ ላይ ከማየት

ይህ እግዚአብሔር እንዲረዳው ሕዝቅያስ ወደ ሰማይ መመልከቱን ያመለክታል፡፡ የዚህ አሳብ ሙሉ ትርጉም በይበልጥ ግልጽ መሆን ይችላል፡፡ አት፡- "ከሰማይ የሚመጣ እርዳታ እጠብቃለሁ' ወይም "እንድትረዳኝ እጠብቅሃለሁ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ)

ተጨንቄአለሁ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "በሽታዬ አስጨንቆኛል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ምን እላለሁ?

ሕዝቅያስ ምንም የሚለው እንዳልቀረው ለማጉላት ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ ይህ በአረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "የምናገረው የቀረኝ ምንም ነገር የለኝም' (አሳብ ገላጭ ጥያቄ ተመልከት)

ቀስ ብዬ ሄዳለሁ

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ እሄዳለሁ የሚለው አኗኗሩን ያመለክታል፡፡ አት፡- "በትህትና እኖራለሁ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

ምክንያቱም በሐዘን ተሸንፌአለሁና

"ምክንያቱም ሐዘንን ጠግቤአለሁና' ወይም "ምክንያቱም በጣም አዝኜአለሁና'