am_tn/isa/38/12.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ሕዝቅያስ የተጻፈ ጸሎቱን ይቀጥላል፡፡

ሕይወቴ እንደ እረኛ ድንኳን ከእኔ ተወገደች ተወሰደችም

ይህ እረኛ ድንኳኑን ከመሬት ከሚያስወግድበት መንገድ ጋር በማስተያየት እግዚአብሔር የሕዝቅያስን ሕይወት በፍጥነት እንደሚፈጽመው ይናገራል፡፡ አት፡- "እረኛ ድንኳኑን እንደሚሸክፍና ተሸክሞ እንደሚሄድ እግዚአብሔር ሕይወቴን ከእኔ ፈጥኖ ይወስዳታል፡፡' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ሕይወቴ ተወገደች

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ሕይወቴን ወሰዳት' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ሕይወቴን እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፣ አንተ ከመጠቅለያው ትቆርጠኛለህ

ይህ ሸማኔ ልብሱን ከመጠቅለያው ከሚቆርጥበትና ከሚጠቀልልበት መንገድ ጋር በማስተያየት እግዚአብሔር የሕዝቅያስን ሕይወት በፍጥነተ እንደሚፈጽመው ይናገራል፡፡ አት፡- "ሲጨረስ ሸማኔ ልብሱን ከመጠቅለያው እንደሚቆርጥ፣ ሕይወቴን በፍጥነት ትፈጽማታለህ' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ትቆርጠኛለህ

በዚህ ውስጥ "አንተ' የሚለው ነጠላ ቁጥር ነው እግዚአብሔርንም ያመልክታል፡፡ (የ "አንተ' ልዩ ልዩ አጠቃቀሞች ተመልከት)

መጠቅለያ

ልብስ ለመሥራት ክሮችን ለማጠላለፍ የሚያገለግል መሣሪያ ነው፡፡

እንደ አንበሳ አጥንቶቼን ሁሉ ሰበረ

በአንበሶች ከተበጫጨቀ ሰውነት ጋር እያስተያየ ሕዝቅያስ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መሆኑን ይናገራል፡፡ አት፡- "ስቃዬ በአንበሶች እንደተበጫጨቅሁ ዓይነት ነበር' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)