am_tn/isa/38/01.md

1.8 KiB

ቤትህን አስተካክል

ይህ አንተ ከሞትክ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ቤተ ሰብህንና በጉዳዮችህ ላይ ኃላፊነት የተሰጣቸውን ሰዎች አዘጋጅ ማለት ነው፡፡ ይህ በይበልጥ ግልጽ ሆኖ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ከሞትህ በኋላ እንዲያደርጉት የምትፈልገውን ነገር በቤተ መንግሥትህ ላሉ ሰዎች መንገር አለብህ፡፡' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

አስብ

ፈሊጣዊ ንግግሩ ማስታወስ ማለት ነው፡፡ አት፡- "አስታውስ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

በታማኝነት በፊትህ እንደ ሄድሁ

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ መሄድ ማለት መኖር ማለት ነው፡፡ ሐረጉ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ መኖር ማለት ነው፡፡ አት፡- "በፊትህ በታማኝነት ኖሬአለሁ' ወይም "በታማኝነት አገልግዬሃለሁ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

በፍጽም ልቤ

በዚህ ስፍራ ልብ የአንድን ሰው ፈጽሞ መሰጠትን የሚወክለውን የውስጥ ማንነትን ያመለክታል፡፡ አት፡- "በውስጥ ማንነቴ ሁሉ' ወይም "ፍጹም በሆነ መሰጠቴ' (ምትክ ስም ተመልከት)

በዓይንህ ፊት መልካም የሆነውን

የእግዚአብሔር እይታ የእግዚአብሔርን ፍርድ ወይም ምዘና ይወክላል፡፡ አት፡- "ደስ የሚያሰኝህን' ወይም "አንተ መልካም ነው ያልከውን' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)