am_tn/isa/35/10.md

1.7 KiB

እግዚአብሔር የተቤዣቸው

"መቤዠት' ማለት "ማዳን' ማለት ነው፡፡ ይህ እግዚአብሔር ያዳናቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ያዳናቸው እነርሱ' (ስማዊ ቅጽል ተመልከት)

የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል

ይህ የሰውን ራስ የሰው ሁለንተና ለማለት ይጠቀማል፡፡ አት፡- "ዘላለማዊ ደስታ ይኖራቸዋል' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

ሐሤትና ደስታ … ኀዘንና ትካዜ

"ኀዘን' እና "ትካዜ' እንደሆኑት ሁሉ "ሐሤት' እና "ደስታ' የሚሉት ቃላት በመሠረቱ ትርጉማቸው አንድ ነው፡፡ በአንድነት የእንዚህን ስሜቶች ከፍተኛ ደረጃ መድረስ ያጎላሉ፡፡ (የሁለት ነገሮች ተመሣሣይነት ተመልከት)

ሐሤትና ደስታ ይቆጣጠራቸዋል

ይህ አንድን ሰው በኃይል ለመቆጣጠር የመቻልን ሰብዓዊ ችሎታ ለእነዚህ ስሜቶች በመስጠት ሕዝቡ በሐሤትና በደስታ እንደሚጥለቀለቁ ይናገራል፡፡ አት፡- "በሐሤትና በደስታ ይጥለቀለቃሉ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)

ኀዘንና ትካዜ ይሸሻሉ

የሰውን የመሮጥ ችሎታ ለእነዚህ ስሜቶች በመስጠት ሕዝቡ ከእንግዲህ ወዲያ ሐዘንተኞችና የሚተክዙ እንደማይሆኑ ይናገራል፡፡ አት፡- "ከእንግዲህ ወዲያ ሐዘንተኞችና የሚተክዙ አይሆኑም' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)