am_tn/isa/35/08.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ቁጥሮች የእግዚአብሔርን ሕዝብ መፃኢ ክብር ገለጻ ይቀጥላሉ፡፡

ቅዱስ መንገድ የሚባል አውራ ጎዳና በዚያ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ቅዱስ መንገድ የሚል ስም ያለው አውራ ጎዳና በዚያ ይሆናል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

አውራ ጎዳና

ይህንን ቃል በኢሳይያስ 11፡16 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ንጹሐንም ያልሆኑ

ይህ ንጹሐን ያልሆኑ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር በመንፈሱ ተቀባይነት የሌለውና የረከሰ አድርጎ የሚቆጥረው ሰው በአካሉ ንጹሕ እንዳልሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ንጹሕ ያልሆኑ ሰዎች' ወይም "በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ሰዎች' (ስማዊ ቅጽልና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በእርሷ የሚሄድባት

ይህ ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ መሄድ መኖርን ያመልክታል፡፡ ይህ የተቀደሰ ሕይወት የሚኖርን ሰው ያመለክታል፡፡ የዚህ አረፍተ ነገር መሉ ትርጉም ግልጽ መሆን ይችላል፡፡ አት፡- "በተቀደሰ መንገድ የሚኖር' ወይም "የተቀደስ ሕይወት የሚኖር' (ፈሊጣዊ ንግግርና እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

በዚያ አይገኙም

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "ማንም በዚያ አያገኛቸውም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የዳኑ

ይህ እግዚአብሔር ያዳናቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አት፡- "የዳኑቱ' ወይም "እግዚአብሔር ያዳናቸው' (ስማዊ ቅጽል ተመልከት)