am_tn/isa/35/05.md

2.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ቁጥሮች የእግዚአብሔርን ሕዝብ መፃኢ ክብር መግለጽ ይጀምራሉ፡፡

የዕውሮች ዓይኖች ያያሉ

"ዕውሮች' የሚለው ዕውሮች ሰዎችን ያመለክታል፡፡ ፈውሳቸውን ለማጉላት በዓይኖቻቸው ተወክለዋል፡፡ (ስማዊ ቅጽልና ተለዋጭ ስም ተመልከት)

የደንቆሮች ጆሮች ይሰማሉ

"ደንቆሮ' የሚለው መስማት የማይችሉትን ሰዎች ይወክላል፡፡ ፈውሳቸውን ለማጉላት በጆሮቻቸው ተወክለዋል፡፡ አት፡- "ደንቆሮች ሰዎች ይሰማሉ' (ስማዊ ቅጽልና ተለዋጭ ስም ተመልከት)

አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል

ሚዳቋ በርቀትና በከፍታ ይዘላል፡፡ አንደ ሚዳቋ መዝለል በፍጥነትና በቀላሉ መንቀሳቀስ ለመቻል ጥቅም ላይ የሚውል ግነት ነው፡፡ አት፡- "አንካሳ ሰው ከፍ ብሎ ይዘላል' (ዘይቤአዊ ንግግር እና ግነትና ማጠቃለያ ተመልከት)

የድዳም ምላስ ይዘምራል

ይህ መናገር የማይችሉትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ ፈውሳቸውን ለማጉላት በምላሳቸው ተወክለዋል፡፡ አት፡- "ድዳ ሰዎች ይዘምራሉ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

ውኃ በምድረ በዳ

ባይባልም እንደተባለ የሚታወቀውን ማሰሪያ አንቀጽ መጠቀም ይቻላል፡፡ አት፡- "ውኃ በምድረ በዳ ይፈስሳል' (መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ ተመልከት)

የሚፋጅ አሸዋ ኩሬ ይሆናል

ይህ የውኃ ኩሬ በጋለ አሸዋ ውስጥ ይታያል ማለት ነው፡፡ የዚህ ዐረፍተ ነገር ሙሉ ትርጉም ግልጽ መሆን ይችላል፡፡ አት፡- "በሚፋጅ አሸዋ ውስጥ ኩሬ ይታያል' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

የጥማት መሬት

በዚህ ስፍራ ደረቅ መሬት እንደ ተጠማ ሰው ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ አት፡- "ደረቅ መሬት' (ግዑዙን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)

የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች

ይህ በደረቅ መሬት ምንጭ ይታያል ማለት ነው፡፡ የዚህ አረፍተ ነገር መሉ ትርጉም ግልጽ መሆን ይችላል፡፡ አት፡- "በጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ይታያል' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ቀበሮዎች

ይህንን በኢሳይያስ 13፡22 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ቄጤማና ሸምበቆ

በደረቅ አካባቢ የሚበቅሉ ተክሎች ናቸው፡፡