am_tn/isa/35/03.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

የደከሙትን እጆች አበርቱ፣ የላሉትንም ጉልበቶች አጽኑ

"የደከሙ እጆች' እና "የላሉ ጉልበቶች' የሚሉት ቃላት የፈራን ሰው ይወክላሉ፡፡ አት፡- "ከፍርሃት የተነሳ እጆቻቸው የደከሙባቸውን አበርቱ፣ ጉልበቶቻቸውም የላሉባቸውን አጽኑ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

ፈሪ ልብ ላላቸው

በዚህ ስፍራ ሰዎች የውስጥ ስሜቶቻቸውን በሚያጎሉ በልቦቻቸው ተወክልዋል፡፡ አት፡- "የፈሩ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

ተመልከቱ

ይህ የአድማጮችን ትኩረት ቀጥሎ ወደ ሚነገረው ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አት፡- "ስሙ'

አምላካችሁ በበቀል፣ በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና

ይህ "በቀል' እና "ብድራት' የሚሉት የነገር ስሞች "ቀጣ' በሚል ማሰሪያ አንቀጽ እንዲገለጹ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በቀል' እና "ብድራት' የሚሉት ቃላት ትርጉማቸው ተመሣሣይ ሲሆን እግዚአብሔር የይሁዳን ጠላቶች የሚቀጣ መሆኑን ያጎላሉ፡፡ አት፡- "ስላደረጉት ነገር አምላካችሁ ጠላቶቻችሁን ይቀጣል' (የነገር ስምና የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)