am_tn/isa/35/01.md

3.1 KiB

ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፣ በረሃውም ሐሴት ያደርጋል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች በመሠረቱ አንድ ትርጉም አላቸው፡፡ እነዚህ ቦታዎች ውኃን ማበብንም ስለገኙ ሰው ደስ እንደሚለው ደስ እንዳላቸው ተገልጾአል፡፡ አት፡- "እንደ ምድረ በዳው ደረቁ ምድር ደስ ይለዋል በረሃውም ሐሴት ያደርጋል' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየትና አጓዳኝነት ተመልከት)

አበባ

በምድረ በዳ የሚገኙ ተክሎች ማበብ እንደ ራሱ እንደ ምድረ በዳው ማበብ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ተክሎቹ ያብባሉ' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)

እንደ ጽጌ ረዳም እጅግ ያብባል

ይህ የምድረ በዳ ተክሎች የሚያብቡበትን መንገድ ብዙ አበባዎች ያሉት ጽጌ ረዳ ከሚያብበት መንገድ ጋር ያስተያያል፡፡ አት፡- "ምድረ በዳው ብዙ አዳዲስ ተክሎችንና ዛፎችን ያበቅላል' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል

ይህ እንደ ሰው ደስተኛ እንደሚሆንና እንደሚዘምር አድርጎ ስለ ምድረ በዳ ይናገራል፡፡ አት፡- "ቢሆንም ይሆናል ሁሉም ነገር ደስ ይለዋል ይዘምራልም' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት)

የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል

ይህ በአደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህ እግዚአብሔር ምድረ በዳውን እንደ ሊባኖስ ታላቅ ማድረጉ ለምድረ በዳው የሊባኖስን ክብር እንደሰጠው ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር የሊባኖስን ክብር ይሰጠዋል' ወይም "እግዚአብሔር እንደ ሊባኖስ ታላቅ ያደርገዋል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽና ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ

ይህ እግዚአብሔር ምድረ በዳውን እንደ ቀርሜሎስና ሳሮን ውብ እንዲሆን ማድረጉ ለምድረ በዳው የእነርሱን ውበት እንደሰጠ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ይታወቃል በሚል ያልተነገረው መረጃ ሊታከል ይችላል፡፡ አት፡- "የቀርሜሎስና የሳሮን ውበት ይሰጠዋል' ወይም "እግዚአብሔር እንደ ቀርሜሎስና ሳሮን ውብ ያደርገዋል' (ስዕላዊ ንግግርና መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉ ተመልከት)

የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ

እነዚህ ሁለት ዐረፍተ ነገሮች በመሠረቱ የሚናገሩት አንድ ነገር ሲሆን ለእግዚአብሔር መገለጥ ላይ አጸንዖት ይሰጣሉ፡፡ (የሁለት ነገሮች ተመሳሳይነት ተመልከት)