1.9 KiB
1.9 KiB
በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ
የእግዚአብሔር መጽሐፍ ማለት እግዚአብሔር የተናገረውን መልእክት የያዘ ማለት ነው፡፡ አት፡- "የእግዚአብሔርን መልእክት በያዘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን በጥንቃቄ አንብብ' (ባለቤትነት ተመልከት)
ከእነዚህ አንዱ
"ከእንስሳቱ አንዱ'
ጓደኛውን የሚያጣ የለም
ይህ በአዎንታዊ አረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እያንዳንዱ እንስሳ ጓደኛ ይኖረዋል' (ድርብ አሉታዊ ተመልከት)
አፉ አዝዞአልና
ለተናገረው አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር በአፉ ተወክሏል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር አዝዞልና' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)
ለስፍራቸውም ዕጣ ጣለላቸው
ይህ እግዚአብሔር እንስሳት የት መኖር እንዳለባቸው መወሰኑ ለስፍራቸው በተጨባጭ ዕጣ እንደጣለላቸው ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "የት እንደሚኖሩ ወሰነ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
እጁም በገመድ ለካችላቸው
ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች ነገሮችን የሚለኩበትን መንገድ ያመለክታል፡፡ አት፡- "ለእንስሳት መኖሪያቸውን ሰጣቸው'
ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ
ከትውልድ እስከ ትውልድ የሚለው ሐረግ ወደፊት የሚኖሩትን የሰዎች ትውልዶች ሁሉ ያመለክታል፡፡ ከትውልድ እስከ ትውልድ የሚለውን ሐረግ በኢሳይያስ 13፡20 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "ለዘላለም' ወይም "ሁልጊዜ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)