am_tn/isa/34/11.md

1.8 KiB

በዚያ ይኖራሉ

"በኤዶም ምድር ይኖራሉ'

ጉጉት

ይህንን በኢሳይያስ 13፡21 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ቁራ

ይህ ትልቅ ጥቁር አሞራ ነው፡፡ በዚህ ምንባብ የተጠቀሱትን አንዳንድ የወፍ ዓይነቶች በትክክል መለየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን፣ ወፎች ሁሉ ሰዎች በሌሉበት ቦታ መኖር ይመርጣሉ፣ ስለዚህ ሰው የሌለበት ቦታ ወይም ምድረ በዳን ይወክላሉ፡፡

በውስጥዋ

"በዚያ፡፡' ይህ ኤዶምያስን ያመልክታል፡፡

በላያዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል

ይህ የኤዶምያስን ጥፋት የሚያስከትል ጠንቃቃ ግንበኛ እንደሆነ አድርጎ ስለ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ምድሪቱን በጥንቃቁ ይለካል፣ ከየት ማፍረስና ማጥፋት እንዳለበት ለመወሰን ይለካታል፡፡' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

መለኪያ ገመድ … ቱንቢ

እነዚህ የግንበኛ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ተመሣሣይ የሆኑ ቃላትን በኢሳይያስ 28፡17 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

መሳፍንቶችዋን … ልዑላንዋን

"የኤዶምያስ መሳፍንቶች … የኤዶምያስ ልዑላን'

ልዑላንዋ ሁሉ ምናምን ይሆናሉ

ይህ ልዑላኑ ንጉሣዊ የሆነ ማኅበራዊ ደረጃቸውን ማጣታቸውን ምናምን ይሆናሉ በማለት አጋኖ ያቀርበዋል፡፡ አት፡- "ልዑላኗ ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ አይገዙም' (ግነትን ማጠቃለያ ተመልከት)