am_tn/isa/34/08.md

2.2 KiB

ለእግዚአብሔር የበቀል ቀን ይሆናል

በዚህ ስፍራ "ቀን' የሚለው በቀጥታ "ቀን' ማለት ሳይሆን አንድ የተወሰነ ጊዜን የሚያመለክት ፈሊጣዊ ንግግር ነው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)

በጽዮን ጉዳይ ብድራታቸውን መልሶ ይከፍላቸዋል

ይህ ማለት አስቀድሞ በኢየሩሳሌም ላይ ላካሄዱት ጦርነት እግዚአብሔር ይበቀላቸዋል ማለት ነው፡፡ አት፡- "በጽዮን ሰዎች ላይ ስላደረጉት እግዚአብሔር የሚገባቸውን ቅጣት ይሰጣቸዋል' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

የኤዶምያስ ፈሳሾች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፣ አፈርዋም ድኝ ይሆናል

ስለ ተቃጠሉና በዝፍትና በድኝ ስለተሸፈኑ ውኃውና መሬቱ ለመጠጥና ምግብ ለማሳደግ የማይጠቅሙ መሆናቸው ፈሳሾቻቸውና ምድራቸው በተጨባጭ ዝፍትና ድኝ እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "የኤዶምያስ ፈሳሾች በዝፍት የተሞሉ ይሆናሉ ምድራቸውም በሚነድድ ድኝና ዝፍት ይሸፈናል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

መሬትዋ … አፈርዋ

"የኤዶምያስ መሬት… የኤዶምያስ አፈር'

ዝፍት

ለረጅም ጊዜ የሚነድድ ወፍራም፣ ጥቁር ነገር፡፡

በሌሊትም በቀንም ይነድዳል

ይህ ሁልጊዜ ማለት ነው፡፡ አት፡- "ሌሊቱንና ቀኑን ሙሉ ይነድዳል' ወይም "ሌሊቱንና ቀኑን ሁሉ ሳያቋርጥ ይነድዳል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ከትውልድ እስከ ትውልድ

"ከትውልድ እስከ ትውልድ' የሚለው ሐረግ ወደፊት የሚኖሩትን የሰዎች ትውልዶች ሁሉ ያመለክታል፡፡ ይህንን ሐረግ በኢሳይያስ 13፡20 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ አት፡- "ለዘላለም' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)