am_tn/isa/34/05.md

2.8 KiB

ሰይፌ በሰማይ ሆና ጠጥታ እስክትረካ ድረስ

እግዚአብሔር ራሱን ሰይፍ እንደታጠቀ ተዋጊ ይገልጻል፡፡ ጠጥታ እስክትረካ የሚለው ሐረግ የእግዚአብሔርን ሰይፍ እንደሚበላና እንደሚረካ ሰው አድርጎ ይናገራል፡፡ በሰማይ ብዙ ጥፋት እንደሚሆንና የእርሱን ፍጻሜ ለመግለጽ እግዚአብሔር ይህን ስዕላዊ መግለጫ ይጠቀማል፡፡ አት፡- "በሰማይ ያሉትን ነገሮች ማጥፋቴን ስፈጽም' (ስዕላዊ ንግግርና ግዑዝን እንደ ሰው ማየትን ተመልከት)

ተመልከቱ

የአድማጮቹን ትኩረት ለመሳብና የተነገሩትን ነገሮች እንዲያስቡ ለማድረግ ይህ ቃል በዚህ ስፍራ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አት፡- "ስሙ' ወይም "በመቀጠል'

ለጥፋት በለየኋቸው ሕዝብ ላይ፣ በኤዶምያስ ላይ ትወርዳለች

በዚህ ስፍራ ትወርዳለች የሚለው የእግዚአብሔርን ሰይፍ ያመለክታል፡፡ ይህ እግዚአብሔር ነገሮችን በሰይፍ የማጥፋቱን ስዕላዊ ንግግር ይቀጠላል፡፡ አት፡- "ላጠፋቸው ለራሴ የለየኋቸውን ሰዎች፣ የኤዶምን ሕዝብ ለመቅጣት እመጣለሁ' (ስዕላ ንግግር ተመልከት)

በኤዶም ላይ

ኤዶም የሚለው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አት፡- "በኤዶም ሕዝብ ላይ' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች በበግም … ስብ ተሸፍናለች

ይህ እንስሳትን እንደሚሠዋ ካህን እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለ መግደሉ ይናገራል፡፡ የካህንን ሰይፍ በመግለጽ ይህን ያደርጋል፡፡ አት፡- "ካህን እንስሳትን እንደሚሠዋ እግዚአብሔር ይሠዋቸዋል፤ ሰይፉ በበግ ጠቦት፣ በፍየልና በአውራ በግ ደምና ስብ ተሞልታለች' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና

"መሥዋዕት' እና "እርድ' የሚሉት ቃላት በማሰሪያ አንቀጽነት ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ብዙ ሰዎችን በባሶራ ይሠዋልና፣ ብዙ ሰዎችን በኤዶምያስ ያርዳልና' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ባሶራ

ይቺ በኤዶምያስ ቁልፍ ከተማ ነበረች፡፡ (የስሞች አተረጓገም መንገድ ተመልከት)