am_tn/isa/34/03.md

1.6 KiB

የሟቾቻው ሰውነት ወደ ውጪ ይጣላል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ማናቸውም የሞቱባቸውን አይቀብሩም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ሟቾቻቸው

ይህ የሞቱ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ አት፡- "የሞቱት' (ስማዊ ቅጽል ተመልከት)

ተራሮች ደማቸውን ይጠጣሉ

"ተራሮች በደማቸው ይሸፈናሉ'

ሰማያት እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህ እግዚአብሔር በሰማይ ላይ የሚያደርገው የመጽሐፍን ጥቅልል ከሚጠቀልል ሰው ጋር ተስተያይቶአል፡፡ አት፡- "አንድ ሰው የመጽሐፍን ጥቅልል እንደሚጠቀልል እግዚአብሔር ሰማይን ይጠቀልላል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ እና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

ፍሬም ከበለስ ቅጠልም ከወይን እንደሚጠውልግና እንደሚረግፍ፣ ከዋክብቶቻቸው ይከስማሉ

ይህ ሰዎች ለዘላለም በዚያ እንደሚኖሩ የሚያስቧቸው በሰማይ ያሉ ነገሮች እንኳን እንደ ቅጠል በቀላሉ እንደሚወድቁ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አት፡- "ቅጠል ከወይን እንደሚረግፍ ወይም የበለስ ፍሬ ከዛፍ እንደሚረግፍ እንዲሁ ከዋክብት ሁሉ ከሰማይ ይወድቃሉ' (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)