am_tn/isa/33/09.md

1.3 KiB

ምድሪቱ አለቀሰች ጠወለገችም

ይህ ያለቅስ እንደ ነበረ ሰው ምድሪቱ ደረቅ እንደምትሆን ይናገራል፡፡ አት፡- "ምድሪቱ ትደርቃለች ተክሎችዋም ይጠወልጋሉ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)

ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም

በዚህ ስፍራ "ሊባኖስ' የሊባኖስን ዛፎች ይወክላል፡፡ ይህ የዛፎችን መጠውለገንና መበስበስን የሚያፍር ሰው እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ አት፡- "የሊባኖስ ዛፎች ጠወለጉ በሰበሱም' (ምትክ ስምና ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)

ሳሮን … ባሳን … ቀርሜሎስ

አንድ ወቅት ብዙ ዛፎችና አበባዎች በእነዚህ ቦታዎች ያድጉ ነበር፡፡

ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ

ይህ ሳሮን ምን ያህል ደረቅ እንደሆነ ከምድረ በዳ ጋር ያስተያያል፡፡

ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ

በዚህ ስፍራ ባሳንና ቀርሜሎስ በዛፎቻቸው ተወክለዋል፡፡ አት፡- "ከእንግዲህ በባሳንና በቀርሜሎስ በሚገኙ ዛፎች ላይ ቅጠል አይኖርም' (ተለዋጭ ስም ተመልከት)