am_tn/isa/33/07.md

2.1 KiB

ተመልከቱ

ይህ ቃል በዚህ ስፍራ በመቀጠል ሊነገር ወደ አለው የሕዝቡን ትኩረት ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በተጨማሪም በዚህ ስፍራ የመጽሐፉን አዲስ ክፍል ለማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አት፡- "ስሙ'

በውክልና የተላኩ

መልእክተኞች

ለሰላም የሚሠሩ መልእክተኞች መራራ ለቅሶ ያለቅሳሉ

ይህ ሰላም በማምጣት ስላልተሳካለቸው ያለቅሳሉ ማለት ነው፡፡ አት፡- "መልእክተኞቹ ሰላም እንደሚሆን ተስፋ አድርገው ነበር ነገር ግን አልተሳካላቸውም ስለዚህም መራራ ለቅሶ አለቀሱ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

መንገዶች ባድማ ሆኑ፣ ተጓዦችም የሉም

ሁለተም ሐረጎች በመንገዶች ላይ ተጓዦች ባለመኖራቸው ላይ አጽንዖት ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ሊጣመሩና በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጹ ይችላል፡፡ አት፡- "ከእንግዲህ ወዲያ ሰዎች በመንገዶች ላይ አይጓዙም፡፡' (አጓዳኝነትና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ቃል ኪዳን ፈረሰ፣ ምስክሮች ተዋረዱ፣ የሰው ልጆችም አልተከበሩም

ይህ ምንባብ በእስራኤል የነበረውን የሥነ ምግባር ውድቀት አጠቃላይ ሁኔታ ያመለክታል ወይም አገሪቱ ከአሦር ጋር አሰተማማኝ የሰላም ስምምነት ማድረግ አለመቻሏን ያመለክታል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ የፈጸመውን ቃል ኪዳን ሰበረ፣ ሕዝቡ የምስክሮችን ምስክርነት ችላ አለ፣ እንዲሁም ሕዝቡ እርስ በእርሱ አልተከባበረም' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)