am_tn/isa/33/05.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለይሁዳ ሕዝብ ይናገራል፡፡

እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ከማንም ይልቅ ታላቅ ነው' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ጽዮንን በፍርድ በጽድቅ ይሞላታል

እግዚአብሔር በፍርዱና በጽድቁ ጽዮንን መግዛቱ ጸዮንን በፍርድና በጽድቅ እንደሞላ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ይገዛል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የዘመንህም መረጋጋት ይሆናል

እግዚአብሔር ሕዝቡን ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረጉ እርሱ ራሱ መረጋጋት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ በዘመንህም የሚለው ቃል ሕይወታቸውን ያመለክታል፡፡ አት፡- "በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ደህንነትህን የተጠበቀ ያደርጋል' (ስዕላዊ ንግግርና ምትክ ስም ተመልከት)

የደህንነት፣ የጥበብና የዕውቀት ብዛት

ይህ እግዚአብሔር የሚሰጣቸውን ነገሮች ያመለክታል፡፡ "ደህንነት' የሚለው የነገር ስም "አዳነ' በሚለው ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጥበብ' እና "ዕውቀት' የተሰኙት የነገር ስሞች በቅጽሎች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አት፡- "የተትረፈረፈ ደህንነት፣ ጥበብና ዕውቀት ይሰጣችኋል' ወይም "ያድናችኋል እጅግም ጠቢብና አዋቂም ያደርጋችኋል' (መቅረታቸው አሳቡን ከመረዳት ስለማያጓድሉ የተዘለሉና የነገር ስም ተመልከት)

የእግዚአብሔር ፍርሃት ሀብቱ ነው

ይህ እግዚአብሔርን መፍራት እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚሰጠው ሀብት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔርን ማክበር እግዚአብሔር የሚሰጥህ ውድ ሀብት ይመስላል' ወይም "እግዚአብሔርን መፍራት እንደ ሀብት ለአንተ ውድ ነው' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)