am_tn/isa/32/14.md

2.9 KiB

ቤተ መንግሥቱ ይተዋልና የብዙ ሰዎችም ከተማ ትለቀቃለችና

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ሕዝቡ ቤተ መንግሥቱን ይተዋልና ብዙውም ሰው ከተማይቱን ይለቅቃልና' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ኮረብታው

ይህ በኮረብታው አናት ላይ የተገነባውን ምሽግ ያመለክታል፡፡ አት፡- "በኮረብታው ላይ ያለ ምሽግ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ኮረብታውና ማማው ዋሻ ይሆናሉ

ይህ ምሽጉና ማማው ዋሻ እንደሆኑ አድርጎ መተዋቸውን ይናገራል፡፡ አት፡- "ኮረብታውና ማማው የተተውና ባዶ ይሆናሉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

የሜዳ አህዮች ደስታ፣ የመንጎችም መሰማሪያ

ይህ እነዚህ እንስሳት በተተውት ምሽጋና ማማ መካከል የበቀለውን ሣር በደስታ ይመገባሉ ማለት ነው፡፡ አት፡- "የሜዳ አህዮችና የበግ መንጎች በዚያ የሚገኘውን ሣር ይበላሉ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ለዘላለም

ይህ ረጅም ጊዜ ለማለት ጥቅም ላይ የዋለ ግነት ነው፡፡ አት፡- "እጅግ በጣም ረጅም ጊዜ' (ግነትና ማጠቃለይ ተመልከት)

መንፈሱ እስኪፈስስብን

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር መንፈሱን እስኪያፈስስ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

መንፈሱ እስኪፈስስብን

እግዚአብሔር መንፈሱን ለሕዝቡ መስጠቱ መንፈሱ በእነርሱ ላይ የሚያፈስሰው ፈሳሽ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "መንፈሱ እስኪሰጠን' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ከላይ

በዚህ ስፍራ ሰማይ "በላይ' እንዳለ ተመላክቷል፡፡ አት፡- "ከሰማይ' (ምትክ ስም ተመልከት)

ፍሬያማው እርሻ እንደ ዱር ይቆጠራል

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ፍሬያማውን እርሻ ከጥቅጥቅ ደን ጋር በማነጻጸር ከመጠን በላይ የተትረፈረፈ መሆኑን ያስተያያል፡፡ አት፡- ሰዎች ፍሬያማው እርሻ እንደ ደን ጥቅጥቅ ብሎ አደገ ይላሉ ወይም ፍሬያማው እርሻ ከመጠን በላይ የተትረፈረፈ ይሆናል (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)