am_tn/isa/32/11.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ተንቀጥቀጡ

ከፍርሃት የተነሳ ተንቀጥቀጡ

በምቾት

"ተማምኖ' ወይም "በደስታ'

ልብሳችሁን አውልቁ ዕራቁታችሁንም ሁኑ

ዕራቁት ማለት ዕርቃንን መሆን ላይሆን ይችላል ነገር ግን ዝቅተኛዎቹን እንደ ውስጥ ልብስ ያሉትን መልበስ ነው፡፡ አት፡- "የክት ልብሳችሁን አውልቁና ዕረቁታችሁን ሁኑ ወይም ቄንጠኛ ልብሳችሁን አውልቁ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ

ይህ የሐዘን ወይም የለቅሶ ተግባር ነው፡፡ አት፡- "ስላዘናችሁ ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ' (ምሳሌያዊ ተግባር ተመልከት)

ስለተወደደችው እርሻ፣ ስለሚያፈራውም ወይን ታለቅሳላችሁ

በሚያፈራው እርሻቸውና ወይናቸው ከሚሆነው ነገር የተነሣ በማዘናቸው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ያለቅሳሉ ማለት ነው፡፡ አት፡- "በተወደደችው እርሻችሁና በሚያፈራው ወይናችሁ ከሚሆነው ነገር የተነሣ ታለቅሳላችሁ' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

እሾህና ኩርንችት

ይህንነ ሐረግ በኢሳይያስ 5፡6 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡

ደስተኞች ቤቶች በነበሩት

ደስተኛ ሰዎች በውስጣቸው ስለነበሩ በዚህ ስፍራ ቤቶች ደስተኞች ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ አት፡- "በነበራችሁባቸው ጊዜ ቤቶቻችሁ ደስተኞች ነበሩ' (ግዑዝ ነገርን እንደ ሰው ማየት ተመልከት)

የፈንጠዚያ ከተማ

"ደስተኛ ከተማችሁ' ፈንጠዚያ የሚለው ቃል ግብዣና ጭፈራ ማለት ነው፡፡