am_tn/isa/30/33.md

1.7 KiB

ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ቦታ ተዘገጅታለች

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "ከቀድሞም ጀምሮ እግዚአብሔር የማቃጠያ ቦታ አዘጋጅቷል' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ማቃጠያ ቦታ

ይህ ሐረግ "ቶፌዝ' የሚለው ቃል ትርጉም ነው፡፡ "ቶፌዝ' በአንድ ወቅት ሰዎች ልጆቻቸውን ለሐሰተኛ አማልክት መስዋዕት አድርገው ልጆቻቸውን የሚያቃጥሉበት በሂኖም ሸለቆ፣ ከኢየሩሳሌም በሰተ ደቡብ የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ ( እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ ተመልከት)

ለንጉሥም ተዘጋጅታለች

ይህ የአሦርን ንጉሥ ያመለክታል፡፡ ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "አግዚአብሔር ለአሦር ንጉሥ አዘጋጃት' (እንደሚታወቅ ታሳቢ የተደረገ እውቀትና ግልጽ ያልተደረገ መረጃ እና አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

ክምር ከእሳት ጋር ተዘጋጅቷል ብዙም እንጨት

እሳት ለማንደድ ክምር ከብዙ እንጨት ጋር ተዘጋጅቷል

የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደ ድኝ ፈሳሽ ያቃጥለዋል

ይህ ክፍል የእግዚአብሔርን እስትንፋስ ክምሩን የሚያቃጥል የእሳት ወንዝ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)