am_tn/isa/30/29.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ኢሳይያስ ለይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል

ዝማሬ ይኖራችኋል

ዝማሬ የሚለው ስም በማሰሪያ አንቀጽ እንዲገለጽ ይህ ክፍል እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ አት፡- "ትዘምራላችሁ'

የተቀደሰው በዓል በሚከበርበት ሌሊት እንደሚሆን

ይህ ዘይቤአዊ ንግግር ምን ያህል ሕዝቡ ደስተኛ እንደሚሆን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

የተቀደሰው በዓል በሚከበርበት

ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የተቀደሰውን በዓል በምታከብሩበት ጊዜ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)

የልብ ደስታ

በዚህ ስፍራ ልብ የሰውን ውስጣዊ ማንነት ይወክላል፡፡ አት፡- "ደስ ይልሃል' (ምትክ ሰም ተመልከት)

ወደ እስራኤል ዓለት … አንድ ሰው እንደሚሄድ

ይህ ዘይቤአዊ ንግግር ሕዝቡ ምን ያህል ደስተኛ እንደሚሆን አጽንዖት ይሰጣል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግረ ተመልከት)

ወደ እስራኤል ዓለት

እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመጠበቅ የሚችል መሆኑ ሕዝቡ የሚወጣበትና ከጠላቶች የሚያመልጥበት ዓለት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "ወደ እስራኤል የመከላከያ ዓለት' ወይም "ለእስራኤል እንደ መከላከያ ዓለት ወደሆነው' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)