am_tn/isa/30/27.md

2.7 KiB

የእግዚአብሔር ስም … እንደምትባላ እሳት

እግዚአብሔር እጅግ መቆጣቱ ታላቅ እሳት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

የእግዚአብሔር ስም ይመጣል

በዚህ ስፍራ "ስም' የሚለው እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር ይመጣል' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

ከንፈሮቹ ቁጣን የሞሉ ናቸው፣ ምላሱም እንደምትባላ እሳት ናት

በዚህ ስፍራ "ከንፈር' እና "ምላስ' የእግዚአብሔርን ንግግር የሚወክሉ ምትክ ስሞች ናቸው፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር በታላቅ ቁጣና ኃይል መናገሩ ምላሱ እሳት እንደሆነ ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ አት፡- "እርሱ ሲናገር ቁጣው ሁሉን እንደሚያጠፋ እሳት ነው' (ተለዋጭ ስምና ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

እስትንፋሱ እንደሚያጥለቀልቅ ወንዝ ነው

ለማጥፋት ያለውን ኃይል በሚመለከት አጽንዖት ለመስጠት ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን አየር ከጎርፍ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ (ዘይቤአዊ ንግግር ተመልከት)

አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው

እግዚአብሔር በአሕዛብን መካከል ሰዎችን መለየቱና ክፉ ሰዎችን ማጥፋቱ እግዚአብሔር አሕዛብን በወንፊት ላይ እንዳስቀመጣቸው ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ ይህ በአዲስ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ አት፡- "እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል የሚገኙ ክፉ ሰዎችን ይለያል ያጠፋልም፡፡' (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

እስትንፋሱ በሕዝብም መንጋጋ የሚሰያስት ልጓም ይሆናል

እግዚብሐር የሰዎች እቅድ እንዲጨናገፍ ወይም እንዲጠፉ ለማድረግ ያለው ኃይል እስትንፋሱ ሰዎችን ከትክክለኛው መንገድ አወጥቶ እንደሚነዳ ልጓም ተደርጎ ተነግሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)

በሕዝብ መንጋጋ እንዳለ ልጓም

ልጓም ሰዎች አንድን ፈረስ ለመቆጣጠርና ለመምራት በራሱ ላይ የሚያስገቡት ነገር ነው፡፡ ልጓም በፈረሱ አፍ ውስጥ የሚገባ ትንሽ ብረት ይኖረዋል፡፡ አት፡- "ልጓም በሰዎች ራስ ላይ' ወይም "ልጓም በሰዎች መንጋጋ ውስጥ' (የማይታወቅ ነገርን ስለ መተርጎም ተመልከት)